Saturday, March 16, 2013

ባንኪ ሙን ሹመት ስጡ? አስጨናቂ ድረስ (ከጉለሌ)

                     መጋቢት 7 ቀን 2005 ዓ.ም.

በሁለቱ ሱዳኖች መሃል በሚገኘው አቢየ ግዛት ለሰፈረው ጦር አዛዥ እንዲሆኑ የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሃፊ ባንኪ ሙን በሳምንቱ መጀመርያ ሌ/ጄ ታደሰ ወረደ ሾሙ ተብሎ በኢ.ቲ.ቪ. የተስራጨዉን ዜና  በስደት የሚገኘው የኢትዮጵያ ሳተላየት ቴሌቪዥንም ይህንኑ ማስተጋባቱ በጣም ገርሞኛል፣ ዜናዎች ከመስራታቸው በፊት ጠቀሜታው ሊጤን ይገባዋል እላለሁ፣ እንደሚባለው ሳይሆን ኢሳት በኢትዮጵያ ምድር የሚሰራጨው ከሞላ ጎደል መሆኑም ይታወቃል፣ ቢሆንም  ለኢትዮጵያ ህዝብ በስፋት የተነገረውንና የሰለቸውን  ዜና አልፎ አልፎ ሾልኮ በሚገባውም  ቢሆን በድጋሚ መንገር ዓላማው ምንድነው? ለዲያስፖራውስ ቢሆን ምን ሊበጀው? ታጋይ ታደስ ወረደ ሲፈልግ ጄኔራል ሲፈልግ የናጠጠ ቱጃር ነጋዴ እየሆነ ላለ ስው አሁን ደግሞ በዓለም አቀፍ መድረክ እውቅና ማግኘቱን ለማስተዋወቅ ካልሆነ በቀር ምን ሊጠቅመው፣በቀልም ትምህርት ደረጃው በውትድርና  ሙያ የተማራቸው ትምህርቶች በግዳጅ አፈፃፀም  ብቃቱ የተሳተፈበት ካለ(በ21 ዓመታት የተፈተኑበት የጦር ሜዳ አለ ማለት አይቻልም፣ የኢትዮ-ኤርትራን  ዓላማ ቢስ ውጊያ እዚህ አይፃፍም) ታሪክ መንገር ተገቢ ይሆን ነበር፣ህዝቡ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ስልችቶት ማየት በማቆሙ በኢሳት በኩል መረጃ ማስተላለፍ  ገንቢ ቢሆንም  ያልተስሙና የህዝቡን ችግርና ብሶት ገላጭ ሊሆኑ ይገባል እላለሁ፣ ይህን መስል ዜናዎች ጥንቃቄ ይደረግባቸው  ህዝብን ያሳስታልና፣ ከትክክለኛ መረጃ ውጭ ያደርጋልና፣ በዜናው መሃል “ሌ/ጄ ታደስ ወረደ የ35ዓመታት ያካበቱት የውትድርና ሙያ ልምድ ለዚህ ሹመት አብቅቷቸዋል ይላል”፣   ወያኔ ኢትዮጵያ ከገባ  21ዓመት መሆኑ እየታወቀ ይቺን እንኩዋን ሳያስተካክሉ እንደወረደ ከኢቲቪ ተቀብለው ማስተላለፍ ትክክል አይደለም፣  የኢትዮጵያ ህዝብ ታጋይ ታደስ ወረደን የሚያውቀው ታታሪ ባለሃብት መሆኑን ነው፣ የተለያዩ ታላላቅ ድርጅቶች ከፍተኛ የአረቦን(ሼር) ባለድርሻ  ከነዚህም የባንክ፣ የቢራ ፋብሪካና የአበባ እርሻ ይጠቀሳሉ፣የታላላቅ ህንፃዎች ባለቤት ሌሎችም ሊኖሩ ይችላሉ፣ በዚህ ዙሪያ ስፊ ዘገባ ማቅረብ ሲቻል ለደሞዝ  ሲባል በየተራ የራሱን ጦር በሱዳን እየተፈራረቀ  የሚያዘውን የወያኔ አባላትን ያውም ከህወሃት ብቻ ማጋለጥ ሲገባ  የባንኪ ሙን የይስሙላ ሹመት መስጠት ታላቅ ዜና መሆን አይገባውም፣
ሌላው አስገራሚው  በአቢየ ግዛት የሚገኘው ስራዊት የኢትዮጵያ ጦር ብቻ መሆኑ እየታወቀ፣ የተ.መ.ድ. ሲባል ተዋፅኦው ከሌላው ዓለም ጭምር አስመስሎታል፣ ይህም የአድማጩን ግንዝቤ ያሳስትል፣ በዚህ ጉዳይ ባለፈው ወር የኢህአዴግ መከላከያ ስራዊት በዓል ሲከበር አጭር ማስታወሻ ፅፌ ነበር በአቢየ ግዛት የስፈረው የኢትዮጵያ የመከላከያ ስራዊት ብቻ ሲሆን በተመሳሳይ በሶማልያም የኢትዮጵያ ጦር ይገኛል፣ በሁለቱም አገሮች ስለሚገኘው ጦር አንድም ግዜ የጉዳት ሪፖርት ቀርቦ አያውቅም፣ ፓርላማው መጠየቅ እንደማይችል ሟቹ መለስ ዜናዊ ብርቱ ማስጠንቀቂያ መስጠታቸው ይታወሳል፣ በሁለቱም አገሮች በየግዜው ጉዳት ስለመድረሱ ግን በተለያዩ ግዜያት በውጭ ሚድያዎች የተዘገበ  ቢሆንም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንም ሆነ ኢሳት ያስተላለፉበት ስዓት አላስታውስም፣ ከኢሳት የሚጠበቀውም ይህን መስል ለህዝብ የራቁ ዜናዎችን አነፍንፎ ማምጣት እንጂ ከኢቲቪ ተቀብሎ ማስተጋባት ወያኔን ካልሆነ በቀር ማንንም አይጠቅምም፣
ሽብርተኛን መዋጋት በሚል ሽፋን በየዓመቱ  ከአሜሪካን መንግስት፣ከአውሮፓ ህብረትና ከአለም አቀፍ የገንዘብ ተቁዋማት ለኢትዮጵያ መንግስት የሚፈስው ገንዘብ የኢትዮጵያን ልጆች ማስጨረሻ የደም ገንዘብ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፣ በርካታ ወገኖችችን መድረሻ አጥተው ስራዊቱን በመቀላቀላቸው በነዚህ ሁለት አገሮች ውስጥ በየዕለቱ እየተቀጠፉ ይገኛሉ፣ ያገር ያለህ እያሉ በስው አገር ዓላማውን ባልተረዱበት ጦርነት ገብተው የምዕራባውያንን ውጊያ ይዋጋሉ፣ አለቆቻቸው ሚሊየነር የሚሆኑበት ስራ ውስጥ መስማራታቸውን እነሱ ግን ህይወታቸው ተርፎ ሲመለሱ እንኩዋን ተገቢው ክፍያ እንደማያገኙ ተገልፁዋል፣ ኢሳት ይህን መስል አቤቱታ ሊያስማላቸው ይገባል፣ በየእለቱ ሊጮህላቸው ይገባል፣ የውጭ ዕርዳታ የሚባለው ገንዘብ ለኢትዮጵያ ዕድገትና ልማት ሳይሆን በተ.መ.ድ. ሚሲዮን ስበብ የወያኔ ሹማምንት መክበርያ መሆኑ ይታወቃል ብዙ ታብሎለታልና ኢሳትም ያለመታከት ይህን ኡኡታ ሊያስማ ይገባል፣
አስጨናቂ ድረስ   (ከጉለሌ)   baschenaki44@gmail.com

8 comments:

David E. Jacobs said...

Very nice and helpful information has been given in this articlehttp://www.promptessay.com/ =))).

ivan koki said...

The best lighting for smart people. Visit our site and ensure the adequacy of price .
Informative and interesting which we share with you so ihttp://www.essays-writings-service.net/
think so it is very useful and knowledgeable. I would like to thank you for the efforts. I am tiring the same best work from me in the future as well. I'll use this information to provide research paper help.

ivan koki said...

Very impressive publication here. Moreover as I see, this question is very actual for many people indeed. Personally I totally agree with author opinion about this subject and I think that it would be really interesting to create such discussion with other this website visitors.http://www.essay-writings-service.com/ Anyway thanks a lot one more time for the great and informative publication. And I will definitely be waiting for more such nice posts like this one from you. Kind regards, Peter Rickson.))

Mari said...

This is an interesting and relevant site. And I advise you to look back here http://essay-writings-service.com/
and appreciate this idea in general ...

Anonymous said...

Such useful post. http://online-essay-writer.org/ I found it very informative.

Anonymous said...

I'd like to thank you for sharing such useful information. http://online-essay-writer.org/ I always read your posts.

Anonymous said...

I always visit your page. http://online-essay-writer.org/ There are many interesting facts.

writing essay said...

You will have a personal figure, that web page blew my own, personal start, even as it appears to be like until this do not own one thing personal. And there's a person hold - was basically it really is article writer, undoubtedly most people don't enjoy this can cause the girl's non-standard house in contrast to the opposite shares knowledge. Nonetheless, fresh nearly anything make sure that, I know he is instigated an important fortune.

Quick Linker

Amazon SearchBox

About the Bloger

My photo

Prof. Muse Tegegne has lectured sociology Change &  Liberation  in Europe, Africa and Americas. He has obtained  Doctorat es Science from the University of Geneva.   A PhD in Developmental Studies & ND in Natural Therapies.  He wrote on the  problematic of  the Horn of  Africa extensively. He Speaks Amharic, Tigergna, Hebrew, English, French. He has a good comprehension of Arabic, Spanish and Italian.